速報APP / 生活品味 / ስንክሳር * Senksar

ስንክሳር * Senksar

價格:免費

更新日期:2019-05-26

檔案大小:8.2M

目前版本:1.4

版本需求:Android 4.0 以上版本

官方網站:mailto:helpfulstudio@gmail.com

Email:https://onesam55.wixsite.com/mysite

聯絡地址:POBOX: 12023 CMC, Addis Ababa, Ethiopia

ስንክሳር * Senksar(圖1)-速報App

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!

ስንክሳር ማለት የእግዚአብሔርን ረድኤት አጋዥ በማድረግ በበጎ ስጦታውም የተሰበሰበ ማለት ነው፡፡

ይህ ሃይማኖቶታቸው የቀና የከበሩ አባቶች ፣ ከቅዱሳን ሰማዕታት ፣ ከጻድቃን ፣ ከነቢያት ፣ ከሐዋርያት ፣ ከሊቃነ ጳጳሳት ፣ ከኤጲስቆጶሳት ፣ ከመነኮሳትም ሁሉ ከገዳማውያንም ከገድሎቻቸው ከመላእከት አለቆችም ከድርሳናቸው የሰበሰቡትና ያቀነባበሩት አምላክን የወለደች እመቤታችን የከበረች ድንግል ማርያም ከአደረገቻቸው ድንቆች ተአምራቶችም የክብር ባለቤት የሆነ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የበዓላቶቹን መታሰቢያ በዘመናት ሁሉ ከመስከረም መባቻ እስከ ዓመቱ ፍፃሜ ሁል ጊዜ ምእመናን እንዲያነቡት እንዲሰሙትም ይሆን ዘንድ ተዘጋጀ፡፡

ይህንንም መጽሐፍ ሰብስበው ያቀነባበሩት በሽህ ሦስት መቶ ንጹሐን በሆኑ ሰማዕታት ዘመን ነው፡፡ የእሊህ የተባረኩ አባቶቻችን ጸሎታቸውና በረከታቸው ከእኛ ጋር ይኑር፡፡

ለዘላለሙ አሜን፡፡

ስንክሳር * Senksar(圖2)-速報App

የቅዱሳንን ታሪክ ለማንበብ ከታሪካቸውም ለመማር እኛም በክርስትና ህይወታችን እንዲሁም በእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴያችን ውስጥ በዋነኝነት ቅዱሳኑ እንዲራዱን እንዲያማልዱንም በሌላም መልኩ ከነሱ የክርስትና ህይወት በመነሳት እኛስ ምን ማረግ እንችላለን ከቅዱሳኑ ታሪክ ምንን እማራለው የሚለውን እንድናስብ ይረዳናል ብሎ በማሰብ እንዲሁም በብዙ መፅሃፈ ስንክሳርን ማግኘት በማይችሉ ምእመናን ጥያቄ መሰረት ይህን የሞባይል አፕሊኬሽን ለራሶ እንዲሁም ከጉዋደኞቾ ፣ ቤተሰቦቾ ፣ የስራ ባልደረቦቾ ባጠቃላይ ከወዳጅ ዘመዶቾ ጋር በመሆን ይጠቀሙበት ዘንድ ትልቁን የቤተክርስቲያን መፅሃፍ መፅሃፈ ስንክሳርን ጠቅለንም ባይሆን ፈጣሪ በፈቀደ የቻልነውን ሙሉውን ታሪክ ያልቻልነውን ደግሞ ዋና ታሪኩን ጨምቀን አቅርበናል፡፡

እርሶም እኝህን መንፈሳዊ ታሮኮች ሰአት መድበው በቀን ቢያንስ ከ3—10 ደቂቃ ወስደው የእለቱን ስንክሳር እንዲያነቡ እንዲማሩበት ከወዳጆቾ ጋርም ውይይቶችን እኒዲያረጉበት እንመክራለን፡፡

ድጋፍዎ አስተያየትዎ አይለየን

ፈጣሪ ከቅዱሳኑ ይደምረን

አሜን!!

ስንክሳር * Senksar(圖3)-速報App

በዚህ እለት ማን ቅዱስ እንደሚከብር ያውቃሉ? ከነ ታሪካቸው ገብተው ይመልከቱ ከበረከታቸውም ተካፋይ ይሁኑ፡፡

ይህንንም ስራ ሰርቶ ለማጠናቀቅ አመታትን የፈጀ ሲሆን በዚህ ስራ ላይ ሃሳብ አስተያየታችሁ ለሰጣችሁ ፣ በመፃፍ ፣ በማስተካከል …. ባጠቃላይ ለረዳችሁን ሁሉ አምላክ ይክፈላችሁ፡፡

ስንክሳር * Senksar(圖4)-速報App